Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ
عربى

አትኩሮቶቻችን

የልጆች አስተዳድግ በኖርዌ

የልጆች አስተዳደግ ከልጆች ጋር ያለንን መልካም የሆነ አጠቃላይ ግንኙነት የሚመለከት ባለ ስምንት ነጥብ ፅንሰ-ሃሳብ ነው።

ከልጅዎ ጋር እንዴት የተሻለ ግንኙነት ሊኖርዎ እንደሚችል ያስባሉ? የወላጆች መምርሄ ፕሮግራም ለዚህ የሚያግዝ ህፃናት ልጆች ላላቸው ወላጆች የሚሆን ባለ ስምንት ነጥብ ጥሩ መመሪያ አዘጋጅቷል።

አወንታዊ ስሜት ኣሳይ፣ ልጅህን እንደምትወድ ኣሳይ
ልጅህን እንደምትወደውና እንደምታፈቅረው እንዲሁም ደስተኛ እንደሆንክና ጉጉት እንዳለህ ማሳየት ለልጅህ የደህንነት ስሜት መሰማት በጣም አስፈላጊ ነው።ምንም እንኳ ትናንሽ ልጆች ንግግር ባይገባቸውም፣ ፍቅር ሲሰጧቸውና ሲከለክሏቸው እንዲሁም ሃዘንና ደስታ ይገባቸዋል።ይሄንን በተለያየ መንገድ ማድረግ ይቻላል እንዲሁም እንደ እድሜኣቸው ኣፈጻጸሙ ይለያያል።

  • ፈገግ ማለት
  • ማቀፍና መሳም
  • ማሻሸት
  • መቀለድና ኣብሮ መሳቅ
  • ለስለስ ባለና በፍቅር ማናገር
  • ምቹና ተገቢ ግዜ ላይ እንደምትወደው መንገር

ለልጁ እንደሚስማማው ሁን እንዲሁም የሱን ፍላጎት ተከታተል
ከልጅህ ጋር በምትሆንበር ጊዜ ልጁ ምን እንደሚዎድ ምን እንደሚያደርግና ምን እንደሚሰማው መታዘብ፣ ይኸውም በልጁ ጫማ ሆኖ ሚሰማውን ሚፈልገውንና ቀልቡ የተያዘበትን መረዳት ያስፈልጋል። እንዲህ ሲሆን ልጁ ስለሱ ግድ እንደሚልህ ይረዳል።

ሁሉም-አዋቂም ሆነ ትንሽ-መታየትንና የሚሉትን ሰው እንዲረዳቸው ይፈልጋሉ።እስከተወሰነ ገደብ ድረስ፣ ሌሎች ሰዎች ገፋፍተውት ከሚያደርግ ይልቅ የራሱን ሃሳብ ቢከተል ይመረጣል ምክንያቱም ይሄ ልልጁ እድገት በጣም አስፈላጊ ነው።እንዳትቸኩልበትና አንተ ብቻ የምትመራው እንዳትሆን ተጠንቀቅ፣ በራሱ ተነሳሽነት እንዲያደርግ ጊዜ ስጠው። ይህ ማለት ግን አንተን እንደፈልገ ሚያዝህ ልጁ ይሁን ማለት ኣይደለም!

  • ልጁ ሲናገርህ መልስለት
  • የልጁን ጨዋታዎችና ድርጊቶች ተከታተል
  • ልጁ ምን እንደሚያደርግና እንደሚፈልግ ተመልከት
  • ብሰውነቱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚል ማወቅ
  • ልጁ ምን እንደሚፈልግና እንደሚሰማው ገምት
  • ልጁ ለሚፈልገውና ለሚሰማው መልስ ስጥ
  • ልጁ እንደሚስማማው ሁንለት
  • ልጁ ለሚይደርገው ፍልጎት አሳይ

    ለልጁ የሚያስባቸውን ነገሮች በተመለከተ ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ

    ገና ከተወለደ ብዙም ሳይቆይ እንኳ በአይን ለዓይን፣በፈገግታ እና በእንቅስቃሴዎች እና በደስታ ድምጾች ስሜታዊ ውይይቶች መጀመር ይቻላል። ልጁ በሚሰራው ወይም በተያዘበት ጉዳይ አዎንታዊ በሆነ መልኩ አስተያየት መስጠት ይችላሉ።ህፃኑ በደስታ ድምጸቶች መልስ ይሰጣል።

    ይህ “ውይይት” ልጅዎ ከእርስዎ ጋር እንዲጣመር፣ ከሌሎች ጋር መሆንን ለመማር እና ጥሩ ቋንቋ ለመገንባት አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም ለትላልቅ ልጆች በግላዊና የቅርብ ንግግር በማድረግ አምነው የግል ጉዳዮቻቸውን ኣስመልክቶ መነጋገር በጣም አስፈላጊ ነው።

    • የጠበቀ ውይይት
    • መቀራረብ
    • አመኔታ እና ምስጢሮች
    • የዓይን ለዓይን ግንኙነት
    • በሰውነት እንቅስቃሴ ተግባቦት መወያየት
    • የአዎንታዊ እንቅስቃሴዎች መለዋወጥና ማስመሰል
    • ሀሳብ፣ ቃላት እና ስሜቶችን እየተለዋወጡ መወያየት

 

ልጅዎ ማድረግ ለቻለው ነገር ሙገሳና እውቅና ይስጡ
አንድ ልጅ አዲስ ነገር ለመሞከር እንዲድፍርና ስለራሱም እምነት እንዲገነባ ልጅዎ ዋጋ እንዳለው መንገርና እና አንድ ነገር ወደ ፍሬያማነት እንዳመጣ መንገሩ አስፈላጊ ነው.።ይህም የሚሆነው መልካም ነገር ሲያደርግ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ነው።ጥሩ ምስጋና ይስጡት፣ ምኑ መልካም እንደሆነ እና ለምን ጥሩ እንደሆነ ይናገሩት። ልጁ በዚያ ዓይነት መታየቱን ማወቅ አለበት። ከዚያም ልጁ ለራሱ ጥሩ ግምት ይኖረዋል።

  • ልጁን ይመልከቱት
  • ዓይን ለዓይን ተገጣጠሙት
  • ልጁን በፈገግታ እና በሰላምታ ይቀበሉት
  • ለምላሽ አዎንታዊ መዳሰስ ይጠቀሙ
  • የቃል ማረጋገጫ ይስጡት
  • ምስጋና እና እውቅና ይስጡ
  • “ጥሩ ነው, መልካም ነው,” ይበሉ። እንዲሁም “ጥሩ ነው, ይህን ስታደርግ, …” እያሉ ለምን ጥሩ እንደሆነ ያብራሩ

የጋራ ተሞክሮዎች ላይ ሃሳቡን ያሰባስቡለት
አብዛኛውን ጊዜ ልጆች ትኩረታቸውን እንዲሰበስቡ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህንም እርስዎ የልጁን ትኩረት በአካባቢያችሁ ወዳሉ ነገሮች በመጠቆም እና በመምራት ሊረዱት ይችላሉ። “እዚህ ተመልከት …” ማለት ይችላሉ እናም ልጅዎ እንዲሰማው ወይም እንዲያየው ወደሚፈልጉት ያሳዩት፣ ወይም እርስዎ ልጁ ወድሚያየውና ትኩረቱን ወደያዘው ማተኮር ይችላሉ። ይህም የሚይስፈልገው እርስዎም ልጅዎም ኣንድ ኣይነት ነገር ላይ አንድታተኩሩ ነው።ብዙውን ጊዜ ግን ልጅ አንድ ነገር ላይ ወላጅ ደሞ ሌላ ነገር ላይ ሲያተኩሩ ይታያሉ።ያለጋራ ትኩረት ደሞ ስለአንድ ነገር ለመነጋገር ወይም አንድ ነገር ለመሥራት አስቸጋሪ ነው።የጋራ ነገር ላይ በጋራ ማተኮር ለጥሩ ግንኙነት እና መግባባት ቅድመ ሁኔታ ነው።

  • ልጁ ምን እንደሚያይ ምን እንደሚፈልግ እና ትኩረቱን የያዘው ምን እንደሆነ በማወቅ የጋራ ትኩረት እንዲኖር ማስቻል
  • የልጁን ትኩረት በመጥራት፣ነገሮችን በማሳየት፣ ዝርዝሮች እና ባህሪያትን በመንገር የጋራ ጉዳያችሁ ላይ ማዞር: “ተመልከት!” “ና!”በሚሉ ቃላት…

በስሜት እና በጉጉት ልምዶችን በመግለጽ ትርጉም ይስጡ
ቃላትን በማስቀመጥ፣ስም በመስጠት እና ነገሮች እንዴት እንደሚሠሩ በማሳየት፣አብራችሁ ለሚያጋጥሟችሁ ስሜትን በማሳየት፣ ህፃኑ አጋጣሚውን ጠቃሚና ትርጉም ያለው ነገር አድርጎ እንዲያስታውስ ያደርገዋል። ህጻኑ በዙሪያው ምን እየተደረገ እንዳለ እንዲረዳ እና እንደ ትርጉም ያለው እና የሚያስደስት ሆኖ እንዲሰማው፣አዋቂዎች ገጠመኞቹን በቃላት ማብራራትና መግለጽ አለባቸው። በዚያህም ልጁ ደህንነት ይሰማዋል። በዚህ መንገድም ለምሳሌ ቋንቋውን ይማራል፣ ከሌሎች ጋር አብሮ መስራትንም ይማራል። ይህ በአብዛኛው የሚከናወነው ከተወለደው ሕፃን ጀምሮ ነው፡ለምሳሌም “እነሆ አሁን ዳይፐር እንለውጣለን፣መቀመጫህ ቆሰለ እንዴ?”

  • ከልጅዎ ጋር በጋራ ስላሳለፋችሁት ገጠመኝ ያውሩ
  • ለምታዩት ነገር ስም መስጠት እንዲሁም ይግለጹት
  • ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ አሳይ
  • አብራችሁ ለሚያጋጥሟችሁ ሁሉ የጋለ ስሜት እና ጉጉት ያሳዩ

የጋራ ተሞክሮዎችን ያስረዱ እና ያብራሩ

ልጁ በዙሪያው ስላለው ዓለም የበለጠ ማወቅ እንዲችልና በዙሪያው ያለው እንዲገባው፣ ለምን ነገሮች እንዲያ እንደሆኑ ሊነገረው ወይም የሚያብራሩ ታሪኮችን ሊሰማ አስፈላጊ ነው። በትናንሽ ልጆች ውስጥ ልጅዎ ከዚህ በፊት ያጋጠመውን ነገር ከዛሬው ነገር ጋር በማነጻጸር የልጁን ልምድ እና መረዳት ማስፋት ይቻላል። “ስንጎበኝ ታስታውሳለህ? ከዛም ተመልክተናል … ” እያሉ።

ህፃናት እያደጉ ሲሄዱ ታሪኮችን መናገር፣ ማብራሪያ መስጠት፣ ጥያቄዎች መጠየቅ፣ ተመሳሳይነት እና ልዩነቶች መፈለግ ይችላሉ። በዚህ መንገድ ህጻኑ በወቅቱ ከሚያልፈው በላይ እናሳውቀዋለን።ይህ ሁሉ ለልጁ የአስተሳሰብ እድገት አስፈላጊ ነው።

  • ገለፃና ማብራሪያ ይስጡ, አንድ ነገር የሆነበትን ምክንያት ያግኙ እና ይንገሩ
  • ከሌሎች ልምዶች ጋር ተመሳሳይነቶችን እና ልዩነቶችን ማወዳደር
  • ባለፉ እና በወደፊቱ መካከል ግንኙነቶችን ማፈላለግ
  • አብራችሁስለምታደርጉት ነገር ታሪኮችን ይፍጠሩ እና ይንገሩ
  • ስዕሎችን ይሳሉ፣ስዕሎችን ይዩ እና በሚያደርጉት ላይ ተመስርተው ቲያትር ይስሩ

አንድ ላይ እቅድ ያውጡ እና ገደብን አወንታዊ በሆነ መንገድ ያስቀምጡ

ልጆች ራሳቸውን ለመቆጣጠር እና እቅድ ለማውጣት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህም በአብዛኛው አዋቂዎች የልጁን ተነሳሽነት ሳይወስዱ ልጁን በመምራት ማድረግ ይችላሉ። ህጻናት ምንም ያለማሰብ፣ ራስ ወዳድነት እና ከሌሎች ልጆችና አዋቂዎች ጋር የመሆን ደንቦችን ሲጥሱ አዋቂዎች ጣልቃ ገብተው በአወንታዊ መንገድ መወሰን አለባቸው። አንዳንድ ነገሮች ለምን እንደማይፈቀድ ለልጁ ማብራሪያ መስጠት አለበት። ለልጁ እምቢ ብሎም “አይሆንም” ከማለት ይልቅ፣ በአወንታዊ መንገድ መምራት አስፈላጊ ነው፣ምን እንደሚፈቀድ መግልጽና እና ከልጁ ጋር መሆንም ያስፈልገዋል። በአብዛኛው ልጁ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርግ ከወላጅ የሚፈልገው አዎንታዊ ትኩረት አለ።

  • ለልጆቹ እንቅስቃሴዎች ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ ለምሳሌ ልጆቹ በጣም ትንሽ ሳሉ የሚፈሩትን ነገሮች በማጽዳት ያስተዳድሩ
  • ጥቆማ በማቅረብ እና ምን መደረግ እንዳለበት በመጠቆም የልጁን እንቅስቃሴ ይምሩ
  • ልጁ እቅድ እንዲያወጣ ደርጃ በደረጃ ያግዙት
  • በልጁ ፍልጎት ላይ በመመስረት ድጋፍ መስጠት – ልጁ ስራው በራሱ እንደተከናወነ እንዲሰማው ሰራውን ሲጀምረው ተወት ማድረግ
  • ልጁ ሁሉንም ክህሎቶቹን ሊጠቀምባቸው የሚችልበትን ተግባራት በመመደብ በጎ ተግዳሮት ይስጡት
  • በአዎንታዊ መልኩ ለተፈቀደለት ነገር ግልጽ ገደቦችን ያስቀምጡለት። ምን ምን እንደተፈቀደ እን ምን ምን እንዳልተፈቀደ ያብራሩለት
  • ልጁ አንድ ነገር ሲከለከል ማብራሪያ ይስጡት።“ስህተት” ሲሰራ ተለዋጭ እንቅስቃሴዎችን በመጠቆም ያስተካክሉት

በኖርዌይ ውስጥ ስለ ሕፃናት ብዙ መረጃዎች አሉ። ይህ መረጃ የልጆች፣ወጣቶች እና የቤተሰብ መምሪያ (ቡፌታት) መረጃ መረብ ላይ ይገኛል።http://bestill.bufdir.no/pub/familievern/foreldreveiledning/8-tema-for-godt-samspill

ቪዲዮ ስለ ልጆች ኣስተዳደግ

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info