Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ

አትኩሮቶቻችን​ - THI በሚከተሉት የጤና ጉዳዮችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኩራል።

  • ስለ ጸረየሴቶች ግርዛት የሚሰሩ ስራዎች መረጃ

” የሴቶች ግርዛት በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ የሚደርግ በህክምና ያልተደገፈ ትልተላና መቆራረጥን ሁሉ የሚያካትት አጠቃላይ መግለጫ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጉዳትና መወገድን የሚያስከትል ነው።”

የሴቶች ግርዛት በብዙ የአፍሪካና ባንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚዘወተር ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ነው። ኖርዌ ውስጥ የሴቶች ግርዛት ህገ-ወጥ ነው። የኖርዌ ባለስልጣናት ብዙ ፀረ-የሴቶች ግርዛት የሆኑ እርምጃዎችን ወደ ተግባራዊነት አምጥተዋል። ከነዚህም እርምጃዎች ኣንዱ የሴቶች ግርዛት ከሚፈፀምባቸው ኣገሮች ለመጡ ሰዎች የሚሰጥ የመረጃ ኣገልግሎት ነው። ይህ መረጃ የተዘጋጀው በ “Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS)” ሲሆን፣ መረጃውንም ከዚሁ ኣካል ማግኘት ይቻላል። THI ደግሞ ይህን መርጃ ለመጤ ሰዎች ይበልጡኑ የሚገኝ ለማድረግ በሴሚናሮችና ለግለሰቦችም ኣንድ ላንድ በቂ በሆኑ መንገዶች ይሰራል። በተጨማሪም ወደ Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS) ድረ-ገጽ በመሄድ መረጃውን ማግኘት ለሚፈልጉ ይህን ይጫኑ (ሊንክ) ።

  • ስለ ኤች.ኣይ./ኤይድስ መረጃ

ኤች.ኣይ.ቪ የሰውነትን የመከላከል ኣቅም በማዳከም ሰውነታችን ለተለያዩ ህመሞችና ጠንቆች ተጋላጭ አንዲሆን የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤይድስ በ ኤች አይ ቪ ቫይረስ በመጠቃት ሲቆዩ የሚመጣ ሲሆን፣ የተለያዩ መዘዞችን ኣስከትሎ ይመጣል።

  • በኖርዌ ስላለ የልጆች አስተዳድግ

በልጆች ኣስተዳደግ ዙሪያ ብዙ መርጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። ጠቃሚ መረጃ በ ልጆች- ወጣቶችና- ቤተሰብ መምሪያ ድረ-ገፅ
Barneoppdragelse i Norge ላይ ይገኛል።

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info

ይህንን ያጋሩ።: