Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ

ራዕያችን

THI (ትቨርኩልቱረል ሄልስ ኢንፎ) የተሳካ የመረጃ ፍሰት አንዲኖር የሚሰራ በጎ አድራጊ ድርጅት ሲሆን፣ የሚያተኩረውም በመጤ ሰዎችና ከመጤዎችም ጋር ሁነኛ ግንኙነት ባላቸው የጤና ባለሙያዎች ላይ ነው። THI መጤ ሰዎች ኖርዌይ ውስጥ አስፈላጊና ጠቃሚ ጤና-ነክ መረጃዎችን አንዲያገኙ ዓላማና ግቡ አድርጎ ይሰራል።

ጤና-ነክ መረጃዎች በድረ-ገጾች ላይ በጤና ተቋማት፣ በበጎ አድራጊ ድርጅቶችና በተለያዩ ፋውንዴሽኖች በብዛት ይገኛሉ። ይሁን እንጂ፣ ተሞክሮ እንደሚያሳየው ከሆነ፣ ባሁኑ ወቅት እንደዚህ ካለው መረጃ ዉስጥ ኣብዛኛው በበቂ መጠን ለሚበዛው ኖርዌይ ዉስጥ ላለው መጤ አይደርስም።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወለላ ሃይሌ በጤና አገልግሎቶች ዉስጥ በነበረችበት ጊዜያቶች አንደምታውቀው፣ ብዙ መጤ ሰዎች ስለ ኤች አይ ቪ ኤይድስ፣ ስለ ካንሰር ህመምና ህክምና፣ ስለ ያለመጠን መወፈርና ስኳር ለነሱ ሚሆን መረጃዎችን ሲፈልጉ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም ክስተት ነው። መጤዎችን በንደነዚህ ያሉ መረጃዎች ለመድረስ፣ ስራዮ ተብሎ እነሱ ላይ ያተኮረ የመረጃ አሰጣጥ ስራ በርግጥ ያስፈልጋል።

ወለላ ሃይሌ ባለፉት ዓመታት ብዙ ሴሚናሮችንና ርዕሰ-ጉዳይ ተኮር የሆኑ ምሽቶችን ለመጤዎች ያዘጋጀች ሲሆን፣ የተሰራው ስራም ውጤታማ ነበር። ሴሚናሮቹ በተለይ ሚያተኩሩት መጤ በሆኑ የጤና ባለሙያዎች ላይ ነው

THI ከጤና ባሉሙያዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ ይቀጥላል። እንዲሁም በ Helsedirektoratet, NKVTS, HIV Norge, Kreftforeningen, Diabetesforbundet, Bufetat እና በሌሎችም በድረ-ገጾቻቸው ላይ የሚሰጡ በመከላከል ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን በማስተላልፉ ላይ በትጋት ይሰራበታል።

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info

ይህንን ያጋሩ።: