Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ

አትኩሮቶቻችን

የሴቶች ግርዛትና የጤና አገልግሎት

ግርዛት ምንድን ነው?

” የሴቶች ግርዛት በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ የሚደርግ በህክምና ያልተደገፈ ትልተላና መቆራረጥን ሁሉ የሚያካትት አጠቃላይ መግለጫ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጉዳትና መወገድን የሚያስከትል ነው።”

የሴቶች ግርዛት በብዙ የአፍሪካና ባንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚዘወተር ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ነው። ኖርዌ ውስጥ የሴቶች ግርዛት ህገ-ወጥ ነው። የኖርዌ ባለስልጣናት ብዙ ፀረ-የሴቶች ግርዛት የሆኑ እርምጃዎችን ወደ ተግባራዊነት አምጥተዋል። ከነዚህም እርምጃዎች ኣንዱ የሴቶች ግርዛት ከሚፈፀምባቸው ኣገሮች ለመጡ ሰዎች የሚሰጥ የመረጃ ኣገልግሎት ነው። ይህ መረጃ የተዘጋጀው በ “Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS)” ሲሆን፣ መረጃውንም ከዚሁ ኣካል ማግኘት ይቻላል። THI ደግሞ ይህን መርጃ ለመጤ ሰዎች ይበልጡኑ የሚገኝ ለማድረግ በሴሚናሮችና ለግለሰቦችም ኣንድ ላንድ በቂ በሆኑ መንገዶች ይሰራል። በተጨማሪም ወደ Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS) ድረ-ገጽ በመሄድ መረጃውን ማግኘት ለሚፈልጉ ይህን ይጫኑ (ሊንክ) ።

ግርዛትን መከላከልና የተገረዙትን በህክምና ማገዝ
ከዚህ ቀጥሎ ያለው ከጤና መምሪያ የተገኘ ነው።
የጤና ባለሞያዎች በሚከተሉት ላይ እንዲያግዙ ይጠበቃል፡

  • ግርዛት ተፈጻሚ ከሆነባችው አገሮች የሆኑ ሴቶች እንዳይገረዙ መከላከል።
  • የሚመለከታቸው ሰዎች ግርዛትን አስመልክቶ ህግ መጣስ መሆኑን፣በጤና ላይ ሰለሚያስከትለው መዘዝ እና የተገረዙ ሊያገኙ ስለሚችሉት ህክምና ጥሩ መረጃ እንዲኖራቸው ማገዝ።
  • በግርዛት ሳቢያ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በወቅቱ ግልጋሎቱን እንዲያገኙ ማገዝ።

ግርዛትን አስመልክቶ በሚደረግ ንግግር ጥሩ መግባባትና ግንኙነት እንዲኖር ያስፈልጋል። ባለጉዳዩ የኖርዌጅያን ቋንቋ እጥረት ካለበት ተርጓሚ ማዘዝ ያስፈልጋል
የበለጠ እዚህ ያንቡ https://helsedirektoratet.no/asylsokere-flyktninger-og-innvandrere/forebygging-og-behandling-av-kjonnslemlestelse

እንዲሁም ይህን ይመልከቱ Lokalt mot: Lokalt samarbeid mot æresrelatert vold, tvangsekteskap og kjønnslemlestelse.

ይህን በማስመልከትም የTHI ሥራ ኣስኪያጅ ወለላ ሃይሌ በግርዛት ላይ ያላትን የስራ ልምድ ታካፍላልች  https://vimeo.com/helsekompetanse/review/195588752/9656732f6f

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info