Norsk English አማርኛ ትግርኛ አዲሱ ኮሮናቫይረስ [coronavirus (COVID-19)] አዲሱ ኮሮናቫይረስ [coronavirus (COVID-19)] አዲሱ ኮሮናቫይረስ ብዙ ትኩረት እየሳበ ነው። ኮሮናቫይረስ በሽታ በተለምዶ መደበኛ የሆኑ ምልክቶችንብቻ ያሳያል። አንዳንድ ሰዎች፣ በተለይ ዕድሚያቸው የገፉ ሰዎች እና አስቀድመው የታመሙ ሰዎች፣በጣም ሊታመሙ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ በሕዝብ መካከል የወረርሽኙን ስርጭት መግታት የሁሉምሰው እገዛ ወሳኝ ነው።በወረርሽኙ የተያዙ ከሆኑ፣ ምልክቶቹ ለመታየት ከ 0 እስከ 14 ቀናት ድረስ ሊወስዱባቸው ይችላሉ።በተለምዶ ከ 5 እስከ 6 ቀናት ያህል ይወስዳል። ምልክቶቹን በሚያሳዩበት ወቅት ሰዎች የማስተላለፍአዝማሚያቸው ከፍተኛ ነው። • ትኩሳት፣ ማሳል፣ እና የአተነፋፈስ ችግር በጣም ከተለመዱት ምልክቶቹ ውስጥ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች የሳንባ ምች፣ የመተንፈስ ችግር ወይም ሌሎች አሳሳቢ ችግሮችን ያሳያሉ።ወረርሽኙን ለመከላከል ጠቃሚ ምክሮች፦ርቀትዎን ይጠብቁ!• የታመሙ ከሆነ ከቤት እንዳይወጡ።• የተነገርዎት ከሆነ በቤት ውስጥ ይቆዩ (በተከለለ ወይም የተነጠለ ቦታ)።• የሚቻል ከሆነ፣ በእርስዎ እና በሌሎች ሰዎች መካከል ቢያንስ አንድ ሜትር ያህል ርቀትዎንይጠብቁ።መልካም የሆነ የእጅ ንጽሕና አጠባበቅ ይከተሉ! እጆችዎን ብዙ ጊዜ እና ሙሉ ለሙሉ ይታጠቡ በተለይ• ከሌሎች ሰዎች አቅራቢያ በሚሆኑበት ሰዓት• ወደ ሽንት ቤት በሚሄዱበት ሰዓት• ሲያስሉ፣ ሲያስነጥሱ ወይም አፍንጫዎን የተጠረጉ ከሆነ• ከማብሰልዎ ወይም ከመብላትዎ በፊት።• ሳሙና እና ውሃ የማይገኝ ከሆነ ሳይኒታይዘር ይጠቀሙ።መልካም የሆነ የአተነፋፈስ ንጽሕና አጠባበቅ ይከተሉ!• ሌሎች ሰዎች ላይ ማስነጠስ ወይም ማሳል ያስቀሩ።• ሶፍት ላይ ያስሉ እና ፍሶፍቱን በጥንቃቄ ይጣሉት። ከዚያ በኋላ እጆችዎን ይታጠቡ!• በቅርብዎ ሶፍት የሌለ ከሆነ፣ ክርንዎ መካከል ያስነጥሱ።ተይዣለሁኝ ብለው የሚያስቡ ከሆነ፦• በበሽታው ተይዣለሁኝ ብለው ያሰቡ ከሆነ፣ በቤት ውስጥ መቆየት አለብዎ። የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ መጀመሪያ ላይ በስልክ ሐኪምዎን ለማግኘት መሞክር አለብዎ። ያ የማይቻል ከሆነ፣ 116 117 ላይ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ላይ ይደውሉ።እራስዎን በቅርብ መረጃ በማግኘት ነቅተው ይጠብቁ!• መንግስት ባለስልጣናት ማንኛውም በኖርዌይ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚቆይ ሰው አስፈላጊውን መረጃ እና በ www.fhi.no እና www.helsenorge.no ላይ ስለ ኮሮናቫይረስ የተሰጠውን ምክር እንዲያነብ ይጠይቃሉ። ምክሩ በየጊዜው ይቀያየራል። መረጃው በሁለቱም ኖርዊጂያንኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ ይቀርባል። ማንኛውም ነገር የመረዳት ችግር ያጋጠምዎት ከሆነ፣ እርዳታ ለማግኘት የሆነ የሚያውቁትን ሰው ይጠይቁ። የበሽታ መተላለፍን ለመከላከል የሚያግዙ ልማዶች እቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ለተነገራቸው ሰዎች በሙሉ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ያገኛሉ www.fhi.no ተጨማሪ መረጃ ከ HivNorway ስለ ኤች አይ ቪ እና ኮሮና: ኮሮና ቫይረስ እና ኤችአይቪ ስለ ኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒክ ወቅታዊ መረጃበሆስፒታሎች ውስጥ ለኤች.አይ.ቪ እና ለኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጠው ክፍል አንድ ከመሆኑ የተነሳ የአብዛኞቹ ሆስፒታሎች የዚህ ህክምና ሰጪ ክፍሎች በስራ ተወጥረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ኤች አይ ቪ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ለአስፈላጊ ክትትል ፣ የመድኃኒት ማዘዣ ለማሳደስ እና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ መሆን ይችላሉ ፡፡ በዚ ያግኙን THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO Organisation no.: 916497997Contact person: WOLELA HAILE – MANAGERTel.: +47 936 019 48Adress: Brugata 1, 0186 OsloE-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info SHARE: Facebook Twitter