Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ
عربى

አትኩሮቶቻችን

ተጨማሪ መረጃ ከ HivNorway ስለ ኤች አይ ቪ እና ኮሮና: 

በሆስፒታሎች ውስጥ ለኤች.አይ.ቪ እና ለኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጠው ክፍል አንድ ከመሆኑ የተነሳ የአብዛኞቹ ሆስፒታሎች የዚህ ህክምና ሰጪ ክፍሎች በስራ ተወጥረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ኤች አይ ቪ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ለአስፈላጊ ክትትል ፣ የመድኃኒት ማዘዣ ለማሳደስ እና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ መሆን ይችላሉ ፡፡

ኢንፎርሜሽን ስለ ኤች.ኣይ.ቪ/ኤይድስ

 • ኤች.አይ.ቪ ምንድነው?

  ኤች.አይ.ቪ (human immunodeficiency virus) ለሚለው ምህፃረ-ቃል ነው። ባንዳንድ ቆየት ያሉ መጽሃፍት ላይ HTLV-III እና LAV ተብሎ ተጠቅሶ ይገኛል። ባሁኑ ጊዜ ግን HIV ተብሎ ነው ሚታውቀው። ይህ ቫይረስ የሰውነትን የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም የተውሰነ ክፍል የሚያጠቃ ነው። ቫይረሱ ሰውነት ውስጥ ሲገባ፣ ሰውነታችን እንደ ባክቴሪያ፣ ቫይረስና ፈንጊ ባሉት ላይ ያለውን የመከላከል አቅም ያዳክማል።

  ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ቆየት እያለ ሲመጣ፣ ብዙ ኤች.አይ.ቪ ተሸካሚዎች በማንኛውም አጋጣሚ-ጠባቂ ህመም ሊጠቁ ይችላሉ። እነዚህ ኣጋጣሚ-ጠባቂ በሽታዎች ባብዛኛው ሰው ውስጥ ያሉ ግን ድብቅ ሆነው የሚተኙና የሰውነት የተፈጥሮ የመከላከል ህዋሳት በትክክል እስከሰሩ ድረስ ምንም የጤና እንከን ማምጣት የማይችሉ ናቸው። ለምሳሌ የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ ሶኮፕላስሞስና ኣንዳንድ ካንሰሮችን መጥቀስ ይቻላል።

   

የኤች.አይ.ቪ ኢንፌክሽን ደርጃዎች

በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የተያዘ ሰው የኤች.አይ.ቪ ተሸካሚ ነው። ህመሙ ምልክት የሚያሳይ ወይም ምልክት የማያሳይ ሊሆን ይችላል። በኤች.አይ.ቪ መያዝን በተለያዩ ደረጃዎች መክፈል ይቻላል፥

 • አጣዳፊ ኤች.አይ.ቪ፡ኣብዛኛው ሰው ፣ ግን ሁሉም ማለት ኣይደለም ቫይረሱ በያዘው ባጭር ጊዜ(ከ 3-6 ሳምንት) ኢንፍሎንዛ የመሰለ አጣዳፊ ምልክት ያሳያል። የተለመዱት ምልክቶችም ትኩሳት፣ በመዋጥ ጊዜ መቸገር(የመዋጫ ሀመም) እና የሊምፍ እጢ እብጠትናቸው።በተጨማርም ድካም፣ ሳል እና ቶንሲል ሊታዩ ይችላሉ።

 • ምልከት አልባ ኤች.አይ.ቪ፡ከዚያ በኋላ፣ አብዛኛው ኤች.አይ.ቪ ተሸካሚ ያለምንም ምልክት ለብዙ ዓመታት ይቆያል። ቢሆንም አንዳንድ ሰዎች ተለቅ ተለቅ ያሉ እባጮች በብዙ የሰውነት ክፍላቸው ሊያሳዩ ይችላሉ።

 • ምልከት ስጭ ኤች.አይ.ቪ፡ቆይቶ፣ በመሠረቱ ከብዙ ዓመታት በኋ፣ በ ኤች.አይ.ቪ የተያዘው ሰው ክብደቱ ሊቀንስና የሚከተሉትም ሊያጠቁት ይችላሉ፥ ሌሊት ሌሊት ማላብ፣ መዛል፣ እባጮች፣ ተቅማጥ፣ ፈንግስ መያዝ (በአፉ ውስጥ)፣ ችፌ ወ.ዘ.ተ። ብዙ ሰዎች ደሞ ምንም ምልክት ሳያሳዩ ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የመሆኛ መንገድ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ማድረግ ነው።

 •  ኤይድስ ምንድን ነው?

ኤይድስ (acquired immunodeficiency syndrome) ለሚለው ምህፃረ-ቃል ነው።ሲንድሮም የሚለው ቃል አንድን አይነት ህመም ወይ ሥቃይ የሚያመለክቱ በዛ ያሉ ምልክቶች ማለት ነው።ኤይድስ በዛ ያሉ በሽታዎችን ሊያመለክት የሚችል ሃሳብ ሆኖ፣ ሁሉም ግን በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ከመያዝ የተነሳ መተፈጠረ የተፈጥሮ የመከላከል ሃይል መዳከም ሳቢያ የሚከሰቱ ናቸው።

የምርመራ ውጤት ኤይድስ ነው የሚባለው ምን ሲያሳይ ነው?

የምርመራ ውጤትን ኤይድስ ነው ለማለት የሚደረጉ መስፈርቶች ካገር አገር ይለያያሉ። ሁንኛ መለያው የኣጋጣሚ-ጠባቂ በሽታዎች በተደጋጋሚና ባስጊ ሁኔታ መከሰት ነው።ከኤች.አይ.ቪ ተሸካሚነት ወደ የኤይድስ ህመምተኛነት የሚደረገው ሽግግር ከጊዜ ጋር የሚያድግ ነው። ባብዛኛው ግን ያንድ ኣሳሳቢ ወይም የብዙ ትናንሽ በሽታዎች መከሰት ኤይድስ መከሰቱን ያሳያሉ።

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info