Norsk English አማርኛ ትግርኛ አትኩሮቶቻችን - THI በሚከተሉት የጤና ጉዳዮችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኩራል። ስለ ጸረ–የሴቶች ግርዛት የሚሰሩ ስራዎች መረጃ ” የሴቶች ግርዛት በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ የሚደርግ በህክምና ያልተደገፈ ትልተላና መቆራረጥን ሁሉ የሚያካትት አጠቃላይ መግለጫ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሴቶች ጾታዊ የአካል ክፍሎት ላይ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጉዳትና መወገድን የሚያስከትል ነው።”የሴቶች ግርዛት በብዙ የአፍሪካና ባንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚዘወተር ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ነው። ኖርዌ ውስጥ የሴቶች ግርዛት ህገ-ወጥ ነው። የኖርዌ ባለስልጣናት ብዙ ፀረ-የሴቶች ግርዛት የሆኑ እርምጃዎችን ወደ ተግባራዊነት አምጥተዋል። ከነዚህም እርምጃዎች ኣንዱ የሴቶች ግርዛት ከሚፈፀምባቸው ኣገሮች ለመጡ ሰዎች የሚሰጥ የመረጃ ኣገልግሎት ነው። ይህ መረጃ የተዘጋጀው በ “Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS)” ሲሆን፣ መረጃውንም ከዚሁ ኣካል ማግኘት ይቻላል። THI ደግሞ ይህን መርጃ ለመጤ ሰዎች ይበልጡኑ የሚገኝ ለማድረግ በሴሚናሮችና ለግለሰቦችም ኣንድ ላንድ በቂ በሆኑ መንገዶች ይሰራል። በተጨማሪም ወደ Nasjonalt kunnskapssenter om vold og traumatisk stress (NKVTS) ድረ-ገጽ በመሄድ መረጃውን ማግኘት ለሚፈልጉ ይህን ይጫኑ (ሊንክ) ። ስለ ኤች.ኣይ.ቪ/ኤይድስ መረጃ ኤች.ኣይ.ቪ የሰውነትን የመከላከል ኣቅም በማዳከም ሰውነታችን ለተለያዩ ህመሞችና ጠንቆች ተጋላጭ አንዲሆን የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤይድስ በ ኤች አይ ቪ ቫይረስ በመጠቃት ሲቆዩ የሚመጣ ሲሆን፣ የተለያዩ መዘዞችን ኣስከትሎ ይመጣል። በኖርዌ ስላለ የልጆች አስተዳድግ በልጆች ኣስተዳደግ ዙሪያ ብዙ መርጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። ጠቃሚ መረጃ በ ልጆች- ወጣቶችና- ቤተሰብ መምሪያ ድረ-ገፅBarneoppdragelse i Norge ላይ ይገኛል። በዚ ያግኙን THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO Organisation no.: 916497997Contact person: WOLELA HAILE – MANAGERTel.: +47 936 019 48Adress: Brugata 1, 0186 OsloE-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info ይህንን ያጋሩ።: Facebook Twitter Google-plus