Norsk
English
አማርኛ
ትግርኛ

ስለኛ

ትቨርኩሉቱረል ሄልሰ ኢንፎ በ 2015 የበጋው ወራት ላይ በ ወ/ሮ ወለላ ሃይሌ ተመሰረተ።

ወለላ ሃይሌ በማህበራዊ የጤና ጥናት(Public Health) የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ ) ከ ኦስሎ ዩኒቨርሲቲ አግኝታለች። የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ፅሁፏ (Thesis) በመጤ ሰፋሪ ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ የሆኑ ሴቶች እና በጤና ባለሙያዎች መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በአስተርጓሚዎች አጠቃቀም ላይ  የሚያተኩር ነበር። በዚሁ ባደረገችው ጥናትና ዳሰሳ ላይ ወለላ በነዚህ ህመምተኞችና በጤና ባለሞያዎች መካከል ያለው ግንኙነት የመግባባት ችግሮች ያሉበት፣የገዘፈ የመረጃ እጥረት ያሉበትና በአስተርጓሚዎች የመጠቀም ሁኔታዉም ውስን እንደሆነ  ለማሳየት ችላለች።

ወለላ በተጨማሪም ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የጤና ዘርፎች ውስጥ ሰርታለች። በነዚህ ዓመታት ያጋጠማት ነገር  መጤ ሰፋሪዎችና የነሱ የቅርብ ሰዎች
በበቂ ሁኔታ ተገቢ መረጃ እንደማያገኙ ነው።ባንዳንድ አጋጣሚዎችም የተሳሳተ መረጃ በመኖሩ ለተሳሳተ ህክምና የዳረጉ ሁኔታውች ተከስተው፣ ለታማሚዎችና ለቅርብ ሰዎቻቸው ከባድ መዘዝ አስከትለዋል። ስለዚህም ነው ወለላ THI መጤ ሰዎች ኖርዌይ ውስጥ አስፈላጊና ጠቃሚ ጤና-ነክ መረጃዎችን አንዲያገኙ የማሳለጥና የማስተባበር ስራ እንዲሰራ የምትፈልገው።

THI ባሁኑ ጊዜ 25 አባላት፣ሁለት የቦርድ አባላት፣አንድ የቦርድ ሰብሳቢና አንድ ስራ አስኪያጅ ያሉት ድርጅት ነው።

በዚ ያግኙን

THI – TVERRKULTURELL HELSEINFO 

Organisation no.: 916497997

Contact person: WOLELA HAILE – MANAGER

Tel.: +47 936 019 48

Adress: Brugata 1, 0186 Oslo

E-mail: wolela@tverrkulturellhelse.info

ይህንን ያጋሩ።: